Wednesday, December 26, 2018

ለተከበሩ ዶ/ር አብይ አህመድ (የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስተር)




በመጀመርያ ለርስዎ ያለኝ አክብሮት መግለፅ እወዳለሁኝ፡፡ እየሰሩት ያሉት ጉዳይ በኔ ዕውቀት የፈጣሪ ካልሆነ በስተቀር እንደ እርስዎ በኢትዮጵያ የአገር መሪ በሌላ አገር የታሰሩትን ዜጎት ስያስፈታ ያየሁት (ያየሁት)፤የሰማሁትም ሰእርስዎ ብቻ ነው፡፡ አሁንስ ተለምኜ የነፈግሁት (አሻፈረኝ ያልሁትን) ስልጣን አማረኝ፡፡ ስልጣን ለህዝብ ማገልገል ሲውል ለኔ ገነት (በገነት ባላምንም) እንደ መግባት ነው፡፡ አንድ መልእክት ግን አለኝ፤ በዘበነ ኢህአዴግ ስልጣን አግኝቼ የኢትዮጵያ ህዝብ ማገልገል ባልችልም ግብር ከፋይ ነኝና የምጠይቅዎት ጉዳይ 5 ደቂቃ ቢያስቡበት ለአምስት ዓመት የኢትዮጵያ ህዝብ ያመስግንዎታል፡፡ ጥያቄና ምስገናዬ፡ ወሬ ሳላበዛ፤ በሰው አገር በእስር ቤት የነበሩ ወንድምና እህቶቻችን ስፈታትዎ ፈጣሪዎ ለኢትዮጵያ ህዝብ ከዚህ የተሻለ እንዲሰሩ ይርዳዎት፡፡ ጥያቄ ግን አለኝ፡ ከተቻለ ሁሉም፤ ካልሆነ በነዚህ ኢትዮጵያውያን የታሰሩባቸው አገራት ያሉ አምባሳደሮች ብያንስ በጡሮታ አሰናብተው፡ በነካ እጅዎ የተሻለ ሰው ይሽሙበት፡፡ አዛውንቶች ስለ ሆኑም ለጤንነታቸው ሲባልም እረፍት ያስፈልጋቸዋልና፡፡ አብዛኛዎቱ በኣገር ውስጥ ህዝብ በድለው ያገኙት ሹመት መሆኑን ያውቁታል ብዬ ነው፡፡ ይህ ስል የኔ ሓሳብ ግምት ውስጥ የሚገባ ከሆነ የኬንያ ኣይመለከትም፡፡ በመቀጠል የዩኒቨርሲቲ ተሻሚዎችን ይፈትሹልን፡፡ በኛ ቋንቋ ተሻሚዎቹ (half-baked academics) ይበዛሉ፡፡ ዩኒቨርሲቲ የቀበሌ አስተዳደር ማድረግያምራቸዋል፡፡

ማሳሰብያ፡ ይህችን ወሬ የምታነቡ ሰዎች በምትወዱት ልለምናቹ፡ ለዶ/ ኣብይና / ወርቅነህ አድርስሉኝ፡፡ በእርግጥ ይህችን ያነበቡ በዘመድ የተሾሙ እንትኖች ልያስሩኝ ይችላሉ፡፡ ኣልፈራም መፅሓፍ ፅፌባቸው እፈታለሁ!!!!
ብየ ነበረ፤ በጉንበት 2010 ዓ/ም

ኣሁን በተወሰነ መልኩ በእርሰዎ ያሳደርሁት እምነት ተሸርሽረዋል እና አላመሰግንዎትም፡፡ የዩኒቨርሲዎች ቦርድ ሀላፊዎች
 
መቀየራቸውም ኣውቀዋለሁ፡፡ ስራዎትን ነው የፈፀሙት፤ ቀድመን እያመሰገን ነው ጉድ የተሰራነው፡፡